ቴዲ አፍሮ የጠበቃውን መግለጫ አወገዘ

የቴዲ ጠበቃ የሆኑት አቶ ሚሊዮን አሰፋ በአገር ውስጥ ለሚታተም (በሳምሶን አሳታሚ) ኢትዮ ቻናል ለተሰኘ ጋዜጣ ደንበኛቸውን ወክለው የሰጡትን መግለጫ አወገዘ፡፡

በኢቲቪ መንግስትን በማወደስ የሚታወቁት ጠበቃው አቶ ሚሊዮን ያለቴዲ ፈቃድ በአገር ውስጥና በውጭ የሚካሄዱና አርቲስቱ እንዲለቀቅ የሚጠይቁ ተቃውሞዎች ‹‹የከሰሩ ፖለቲከኞች ተግባር ነው›› ማለታቸውን አርቲስቱ እንደሚቃውም በቤተሰቦቹ አማካይነት ለደጋፊዎቹ በሙሉ እንዲደርስ ጠይቋል፡፡

ቴዲ በቤተሰቦቹ አማካይነት ባስተላለፈው መልእክት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ ጠበቃው እኔን ወክሎ እንዲነናገር አልፈቀድኩም ብሏል፡፡