የግል ሚዲያ የዴሞክራሲ ዋስትና እንጂ ጠላት አይደለም

ከአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል

[pdf]

ኢትዮጵያ ፈርማ ከተቀበለቻቸው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ሰነዶች አንዱ በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 19 ስር የሚገኘውና ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት የራሱን አስተሳሰብ ስለመያዝ መብቱ የሚደነግገው ክፍል ነው:: ድንጋጌው ሃሳብ በነፃነት የሚገለጽባቸውን የተለያዩ መንገዶች በመብትነት ያጎናፀፈ ሲሆን አጠቃቀሙን አስመልክቶም ግዴታዎችንና ኃላፊነቶችን አካቷል:: … የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 4 ደግሞ ድንጋጌዎቹን የሚያጠነክርና አስፈላጊው የህግ ጥበቃ የሚደረግበትን አግባብ ይገልፃል:: … እድሜ ጠገቡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ህዳር 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በ69ኛ አመት 61ኛ እትሙ አቋሙን ከሚያንፀባርቅበት የርዕሰ አንቀጽ ጎን ቆርኔልዮስ የተባሉ ፀሃፊን መጣጥፍ የአዘጋጆቹ ምንም አይነት ሙያዊ አርትኦት ያልዳሰሰው በሚያስመስል መንገድ የተዘጋጀውን አሳዛኝና አሸማቃቂ ጽሁፍ አስመልክቶ የሚወስነው በመንግስት የተዘጋጀው ኤዲቶሪያል ፖሊሲው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከላይ በተጠቀሰው ዕለት ከድርጊት ዘጋቢነት ይልቅ ወደ ድርጊት አስፈፃሚነት የተለወጡ ጋዜጦችና ጋዜጠኞች በሚል ርዕስ በአውራምባ ታይምስ እና በአዲስ ነገር ጋዜጦች ላይ የቀረበው ጽሁፍ ሃሳብን በነፃነት ከመግለጽ መርህ ይልቅ ከሳሽና ፈራጅ በመሆን በነፃው ፕሬስ ላይ የተቃጣ ስልታዊ ጥቃት ሲሆን የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች አበስራለሁ የሚለው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ይህንኑ ጽሁፍ ከርዕሰ አንቀጹ ጎን ያለውን ገዥ አምድ በመስጠት አትሞ ማሰራጨቱ የጉዳዩን አደገኝነት ያጎላዋል:: … ለመቀጠል እዚህ ላይ ይጫኑ [pdf]