An Orthodox Church priest shot to death in North Shoa

An Ethiopian Orthodox Church priest named Aba Tekle-Mariam, who is the administrator of Kidus Mikael Church in Shenkora Woreda, North Shoa, was shot to death by unknown individuals last week. Aba Tekle-Mariam’s body was hurriedly buried without autopsy.

More in Amharic >>

በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት አንድ አባት በጥይት ተደብድበው ተገደሉ

በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት በሸንኮራ ወረዳ የባልጭ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ተ/ማርያም በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ሪፖርተራችን ዘገበ፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2ዐዐዐዓ.ም. ከቀኑ በ8፡ዐዐ ሰዓት ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ተ/ማርያም ባልታወቁ ግለሰቦች የተገደሉ ሲሆን የሕክምና ምርመራ ሳይደርግላቸው መቀበራቸው ታውቋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ለፓትሪያሪኩ ጽ/ቤት ማመልከቻ የቀረበ ቢሆንም እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም፡፡

Source: ዝክር የዜና አግልግሎት