Rally in Ottawa to oppose Ethio-Sudan secret border deal

Ethiopians in Ottawa, Canada, are organizing a protest rally on May 23, 2008, to commemorate the fallen heroes of May 15 elections, and also to express opposition to the Ethiopia-Sudan secret boarder agreement. More in Amharic >>

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማሰከበርና የግንቦት 2005ን እልቂት ለመዘከር የሚደረግ የሰላማዊ ሠልፍ!

የእናትና አባቶቻችን አጥንት ተከስክሶ፤ ደማቸው ፈስሶ፤ የህይወት መስእትነት ተከፍሎበትና በዚህም ተከብሮ የኖረው የIትዮጵያ ዳር-ድንበር፤ ዛሬ በህወሃት/ኢሕአዴግ አሳፋሪና በታሪክም ምህረት የማይደረግለት ትብብር በሱዳን ወራሪ ወታደሮች ተደፍሯል። ከሰሜን እስከ ደቡብ (ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወለጋና ኢሉባቦር) ባለው አዋሳኝ የሚኖረው ወገናችን፤ አሁንም እንደጥንቱ ተጋዳይ አርበኛ አባቶቻችን ሁሉ የአገሩን ዳር ድንበር ላለማስደፈር
ከሱዳን ጦር ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ በመዋደቅ ላይ ይገኛል።

ግንቦት ላይ ሆነን ግንቦት 1997 (2005)ን በዓይነ-ህሊናችን ስንቃኝ ደግሞ ለኢትዮጵያ ፍትኅና ዴሞክራሲ ለማምጣት ሲታገሉ የወደቁትን ሰማእታት እናስታውሳለን። ምንም እንኳ በህዝባችን መሃል ተገኝተን የመከራው ገፈት ተቋዳሽ ባንሆንም፤ በስደት የምንገኘው እኛ
ወገኖቹ ግን ከጎኑ በመቆም ለዚህ አገሩንና ክብሩን ለማስጠበቅ ቆርጦ ለተነሳውና እየተዋደቀም ላለው ወገናችን ቢያንስ አጋርነታችንንና ድጋፋችንን ልናረጋግጥለት ይገባል።

ስለዚህም እኛ በቶሮንቶ፤ በኦታዋና በሞንትሪያል የምንኖር ኢትዮጵያውያን በአንድነት ስሜትና በቁጥር ብዛት ወጥተን ከቆራጥ እናት-አባቶቻችን፤ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም የወደቁት ሰማእታት ከተሰዉለት ዓላማ ጎን በመሠለፍ፤

1) ወራሪው የሱዳን ጦር ልቡን፤ ዓይኑንና እጁን ከIትዮጵያ ላይ እንዲያነሳ ሰላም ወዳድ የሆኑ የዓለም መንግሥታትን፤ የካናዳን መንግሥትና ህዝብ እንዲሁም ዲፕሎማቶችና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን ለመማጸን፤

2) ለኢትዮጵያ ፍትኅ ለማምጣት በምርጫ 97 እንዲሁም ከዚያም በፊትና በኋላ ሲታገሉ የወደቁትን ወገኖቻችንን አስቦ ለመዋል ሰላማዊ ሠልፍ ጠርተናል።

ስለዚህም የምትችሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በቦታው እንድትገኙልን በታላቅ ትህትና እየጠየቅን፤

ሠልፉ የሚደረግበት ከተማም፡ Ottawa (Canada)
ቀኑ፡ ግንቦት 15፤ 2000 ዓ/ም (May 23, 2008)
ሰዓቱ፡ ከቀኑ 7 ሰዓት (1:00PM) ጀምሮ

የሠልፉ መነሻ ቦታ፡ ከOttawa ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው የህዝብ መናፈሻ
ስለሠልፉ ዝርዝር ጉዞም በመነሻው ቦታ መግለጫ ይሰጣል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ (416) 824-7858 ወይም (613) 867-9292 ይገናኙን
የሠልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ