Columnist Kevin Myers’ article Amharic translation

Ethiopian Review reader Ato Ayele Tena Kassa has translated the controversial article by Irish columnist Kevin Myers as follows.

Dear Editor,

I have read the commentary by Kevin Meyers you posted on July 11th — Africa is giving nothing to anyone — apart from AIDS). I have found it very important that it should also be read in Amharic by your readers. I think this helps us understand how degrading and shameful it is to live on hand out given by Westerners.

Thanks.
Ayele Tena

አፍሪካ ለዓለም ያበረከተችው ነገር ኤድስን ብቻ ነው


በ ኬቭን ሜየርስ (አይሪሽ ኢንዲፐንደንት ኒውስ)
(ትርጉም:- በአየለ ጠና ካሳ)

አይሆንም ሊጠቅምም አይችልም::የአፍሪካ ሃገሮች ዝንባብዌ ላይ ስልጣኔን የተከተለ እርምጃ ለመውሰድ እያንገራገሩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የለማኝ አቁማዳዋን ወደ ምእራባውያን ማዞር ጀምራለች:: አሁንም እንደ አምና እንደገና:: ዝነኛው ቦብ ጌልዶፍ ከ25 ዓመት በፊት “ዓለምን እንመግብ” በሚል የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴን ከጀመረ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ከ33.5 ሚሊየን ወደ 78 ሚሊየን አድጎዋል::

ታዲያ ለምን ሲባል ነው ይህንን አስደንጋጭ የህዝብ ቁጥር እድገት ለማበረታታት ድጋፍና ዕርዳታ የማደርገው ? በምንስ ምክኒያት ?ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክኒያት ሊኖር አይችልም:: እርግጠኛ መሆን ካስፈለገ ምክኒያታዊነት ሊሰራ የማይችልበትን ሁለት ነገሮች ልግለፅ::

አንደኛው የእኔ ምናባዊ አስተሳሰብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የታረዙና የተራቡ ሰዎች ምስል ነው ያው እንደክርሞው አይኑ የፈጠጠ የተራበ ህጻን ዛሬም እንደገና በካሜራ የተቀረጸ ስቃይና ሰቆቃ::

እንደ አብዛኞቻችሁ ሳይሆን እኔ ኢትዮጵያን ጎብኝቻለሁ እንደ አብዛኞቻችሁ ሁሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጠኔን ለማስታገስ የሚያደርጉትን ጥረት አይቻለሁ:: ከሃያ ዓመት በፊት በረሃብ አይኑ ፈጦ ከሞት ያዳነው ህጻን ዛሬ አድጎ ክላሽንኮቭ አንጋች ሆኖ ልቡ እንደፈቀደው ህፃናትንና አዋቂን ገዳይ ጨካኝ ሆኖ አግኝተነዋል:: ካለምንም ጥርጥር ይህንን ፍጹም እርባና ቢስ ነፍሰ በላ የኢኮኖሚ የማህበረሰብና የቤተሰብ ምጣኔ ስርዓት ለማቆየት መከራከሪያ ሊኖር ይችል ይሆናል:: ለእኔ ግን ግልፅ አይደለም በሌላ አመለካክት ይህንን የመሰለ ሂስ ያዘለ ፅሁፍ ላለማቅረብ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ::
አንደኛው ምክኒያት ጠላት እንጂ ብዙም ወዳጅ ሊያተርፍ አይችልም እንዲያውም ከሁሉም በላይ አውቃለሁ ባዮችን ቁጣ የሚቀሰቅስ ነው:: ከዚያም አልፎ በሽሙጥና በግብረገብ የበላይነት የሚያምነው የአየርላንዶችን የኑሮ ዘይቤና ክርክርን የሚመርዝ ሆኖ ምናልባትም በአየርላንድ በጣም የማደንቃቸው እንደ ጆን ኦሺ እና የፈኑካን ወንደማማቾችን የመሰሉ የታወቁ ምሁራንን የሚያስቆጣ ሊሆን ይችል ይሆናል ነገር ግን ቢሆንም ይሁን::

ግን እባካችሁ እናንት ቁጡ ሁሉን አውቃለሁ ባዮች ከዚህ በፊት በአየርላንድ ስለነበረው ረሃብ በሰነፍ ማወዳረሪያ መነፅር አንዳንድ ነጥቦች እንዳነሳ ፍቀዱልኝ::ከዚህ በፊት አየርላንድ ውስጥ በተፈጠረ የረሃብ አደጋ በ20 ዓመት ውስጥ የአየርላንድ ህዝብ ብዛት በ30 ከመቶ በማሽቆልቆል ሲቀንስ በተመሳሳይ ወቅት ግን የምዕራባውያን ምግብ ልገሳ ባለአስር ጎማ ማርሰዲስ ጭነት መኪና እና ሎክሂድ ሄርኩለስ አውሮፕላን ምስጋና ይግባቸውና የኢትዮጵያ ህዝብ በእጥፍ ሊያድግ ችሎዋል::

እንግዲህ ያሳያችሁ ! ይህች የችጋር አገር ከእነ እብደትዋ ብቻዋን እንዳትመስላችሁ እዚያው አካባቢ ከቅስተዳመናው ባሻገር ሶማሊያ የምትባል የጽንፈኞች ክላሽንኮቭ አንጋቢ ጫት ቃሚ ለስራ የሰነፉ እባጮች ይገኛሉ::

በእርግጥ ከሞላ ጎደል አሁን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቅማቸው ለመራባት ብቻ የሆነ መናጢዎች ነፍሳቸውን ማቆየት የቻሉት በምእራቡ ዓለም እርዳታ ስላለ ብቻ ነው::

ይህ ራስን የአለመቻል በሽታ ደግሞ ጥሩ የሆነ የእድገት ፖሊሲ ወይም ፖለቲካዊ አስተዳደር ለመመስረት በውስጣቸውን ማነሳሳት አልቻለም:: እንዲያውም መሃይምነት የሚያመጣው አጉል አምልኮ እድገት እንዲያሻቅብና ከነጭራሹም ይባስ ብሎ የሚቀጥሉት የደቡብ አፍሪካ እጩ ፕሬዝደንትን ከባንባ የሚገኝ የውሃ ጠብታ ሰዎች ብልት ላይ ቢደረግ የነቀርሳ መከላከያ ይሆናል የሚል ተረት ተረት ጠንካራ አማኝ እስከመሆን አድርሶዋቸዋል:: ይህንንም እንተወውና ድህነት ረሃብና የማህበረሰብ መላሸቅ በኤርትራ ኡጋንዳ ኮንጎ ሱዳን ሶማሊያና ኢትዮጵያ የሚደረገውን የመናጢዎች እርስ በርስ ጦርነት ሊገታ አልቻለም::

አንድ ሰዓሊ ልክ በሰፋፊ ብሩሽ አስቀያሚ ደማቅ ቀለም እንደሚጠቀም ሁሉ ታሪክም የብዙ ሃገራትን የአናኑዋር ስዕል ድብልቅልቁን አውጥቶ አጥርቶታል::ከእነዚህም ሃገሮች ውስጥ ጃፓን ቻይና ሩስያ ደቡብ ኮሪያ ቨትናም ፖላንድ እና ጀርመን በ20ኛው ምእተ ዓመት ዛሬ በአፍሪካ ያልታየ ከዚያም የባሰ ስቃይና መከራ አሳልፈዋል:: እነዚህ ሃገራት ናቸው ዛሬ በተዘዋዋሪ መንገድ ለአፍሪካ ዕርዳታ እየሰጡ ወይም አፍሪካ ውስጥ ኢንቨስት እያደረጉ ያሉት::

አፍሪካ ግን ከለም መሬቶችዋና የተፈጥሮ ሃብት ለማንም ልትተርፍ ወይም ልትለግስ አልቻለችም ለአለም የሰጠችውም አንድ ነገር ቢኖር ኤድስን ብቻ ነው::

ይህ በእንዲህ እንዳለ አፍሪካ የተፈጥሮ ሃብትዋን እያባከነች አስደንጋጭ የአካባቢና የተፈጥሮ ውድመት እያደረገች ነው::

በ 2050 የአኢትዮጵያ ህዝብ 177 ሚሊዮን ይደርሳል ይህም ማለት የፈረንሳይ የጀርመንና የቤንሉክስ ህዝብ አንድ ላይ ተደምሮ ማለት ነው:: ይህች ሃገር በታላቁ የአፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ደረቅና ብዙ የማያመርት ቦታ ላይ ትገኛለች::

ስለዚህ ይህንን በሕዝብ ብዛት የተጨናነቀና ያካባቢ ተፈጥሮ ሃብቱን ያወደመ የኢኮኖሚ ተመጽዋች ሃገር መርዳት ምንስ ፋይዳ ይኖረዋል ?
ዛሬ አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ረሃብተኛ ሕጻንን ታድገን ወይም አድነን በቀጣይ አመታት ለዘላለማዊ ድህነት ጦርነት የወሲብ መደፈር አመፅና ጭካኔ ካበቃነው እና እንደገና በአዋቂነት ዘመኑ የራሱን አይነት ግማሽ ደርዘን ጐስቃላ ህፃናትን የሚያበረክት ከሆነ እንደዚህ ያሉትን ሰዎችን ለማዳን ምን ያክል የሞራል ግዴታ ሊኖረን ይገባል ?

በእርግጥ ውስጣዊ ሕሊናችን ጥሩ እንዲሰማን የምናደርገው ሊሆን ይችላል::የዚህ ሁሉ ችሮታም ዋና ምክኒያት ይህ የሚሰማን ስሜት ሊሆን ይችላል:: ነገር ግን ይህም በቂ አይደለም::

በአፍሪካ ለራስ ጥቅም ሲባል የሚደረግ ችሮታ አፍሪካ ላይ ከወረደው እርገማን አንዱ እንጂ ሌላ ሊሆን አልቻለም:: ይህ አይነት ቸርነትና ልገሳ ሕይወት ሊሰጥ የቻለው ካለዕርዳታው ዕድሜ ሊኖራቸው የማይችሉትን እርባና ቢስ የፖለቲካ ስርዓቶችን ብቻ ነው:: የዚህም አይነት እርዳታና ልገሳ የኢትዮጵያንና የኤርትራን ጦርነት ለአስር አመት አካባቢ ከማራዘም ሌላ የፈየደው ነገር የለም::

በታዋቂው ቢልየነር ቢል ጌትስ የተቀየሰው የወባ በሽታን መከላከል መርሃ ግብርን ስናየው በጣም አነሳሳሽና ገንቢ ሃሳብ ቢሆንም ቅሉ በሌላ በኩል ካየነው ደግሞ የግል ዲሲፕሊን (ወሲብን በተመለከተ) ጨርሶ በጠፋበት ዓለም ይህ በሽታ የህዝብ ብዛትን ዕድገት ለመቆጣጠር በጣም ውጤታማ የሆነና አሁን በስራ ላይ ያለ ብቸኛው አማራጭ ነው::

ይህ የቢል ጌትስ መርሓ ግብር ከተሳካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት በጨቅላ ዕድሜ ከመቀጠፍ ይድናሉ በማለት በጉራ ይናገራሉ:: በጣም ጥሩ ግን ከዚያስ? ሁሉም ወደ እኛው ወደ ምእራቡ ዓለም ይምጡ? አዎ ይህም አንድ ሃሳብ ነው::