UDJ press release

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE

Press Release

Unity for Democracy and Justice Party (UDJ), the heir to the former CUDP, wishes to announce to the local and international media community that it is officially ready to operate as a duly registered national party and to launch its programme of activities for the year 2001 (E.C). UDJ has pledged to pursue the goals, objectives and the inspiring vision of CUDP with a new spirit and greater determination.

To achieve its objectives successfully, UDJ needs the support of many sectors of the national society and international community. One of these sectors is the local government and private as well as the international media community. UDJ believes that seeing democracy take root and flourish in Ethiopia is the wish of the government, private and international media. Therefore, it hopes that in its endeavor to contribute its share to the fulfillment of this common cause, it will enjoy the support and cooperation of the media.

The purpose of this first get-together is to share views on how, through concerted efforts, we can complement each other’s contribution to the common cause and avoid communication and interaction problems experienced in the past.

. In view of the fact that working together for mutual benefits and resolving communication problems through dialogue takes time, UDJ has worked out a programme of regular meetings with the media. Today’s meeting is the beginning of the continuous and regular dialogue that UDJ wishes to maintain with the media.

UDJ will contribute its share to enabling multiparty system to flourish in Ethiopia. Even though recent legislations affecting political parties, the press and civil societies threaten to further narrow the political space severely, UDJ believes strongly that if we worked diligently and with determination and patience, it is possible to widen the political space that, we believe, is deliberately being narrowed and to revive the hope of the Ethiopian people to see democracy flourish in their country. UDJ calls upon the Government to contribute its share to the fulfillment of this hope by broadening the political space in a manner that demonstrates responsible leadership.

UDJ wishes to see the media as a true mirror through which it looks at itself and as a cause for continuously correcting and improving itself. It is ready to learn from your insightful editorials and reportings and to be your steady partner in your endeavors to bring reliable information to the people.

Unity for Democracy and Justice

September 25, 2008

Addis Ababa

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ

ጋዜጣዊ መግለጫ

የቀድሞ ቅንጅትን ዓላማና ራዕይ ወርሶ የተነሳው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በቅንጅት የተጀመረውን በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማስፈን ጥረት በአዲስ መንፈስና በአዲስ ተስፋ ለመቀጠል ቆርጦ የተነሳ ለመሆኑ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች አሳውቋል። ትግሉን ለመቀጠል የሚያስችሉ ዝግጅቶችንም አጠናቅቆ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ሕጋዊ እውቅና በማግኘት በፕሮግራሙና በሕገደንቡ መሠረት ለመንቀሳቀስ ተዘገጋጅቷል።

አንድነት ዓላማውን ለማሳካት ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ትብብርና ድጋፍ ያስፈልገዋል። ከእነዚህ ክፍሎች አንዱ የመንግሥትም ሆኑ የግሉ መገናኛ ብዙሓን ቤተሰብ ነው። አንድነት ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ የማስፈን ዓላማ የመንግሥትም ሆነ የግሉ መገናኛ ብዙሓን እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ ዓላማ ነው ብሎ ያምናል። ስለዚህ አንድነት ይህን የጋራ ዓላማ ለማሳካት የበኩሉን ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ከመንግሥትም ሆነ ከግል መገናኛ ብዙሓን ተገቢውን ትብብርና ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ ያምናል። የዛሬው መገናኘታችን ይህን የጋራ ዓላማ ለማሳካት ሁላችንም በምናደርገው ጥረት እንዴት መደጋገፍ እንደምንችል፤ ከአለፈው ልምዳችን የታዩ የአሠራርና የአካሄድ ችግሮች ካሉ እንዴት ሊወገዱ እንደሚችሉ ሃሳብ ለመለዋወጥና ለመወያየት ነው። ይህ የዛሬው ግንኙነታችን የመጀመሪያ እንጂ የጨረሻ አይደለም። ተባብሮ መሥራትና ችግሮችን በውይይት ማስወገድ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ አንድነት ከመንግሥም ሆነ ከግል መገናኛ ብዙሓን ጋር እየተገናኘ የሚወያይበት ቋሚ ፕሮግራም አውጥቷል። የዛሬው ግንኙነታችን የዚህ ቋሚ ፕሮግራም የመጀመሪያው ርምጃ ነው።

በዚህ አጋጣሚ አንድነት የአጭርና የረጅም ጊዜ የሥራ ዕቅዶችን አውጥቶ ለመንቀሳቀስ አስፈላጊውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል። ዝግጅቱ ድርጅታዊ መዋቅርን በየደረጃው ከመዘርጋትና ከማጠናከር ጀምሮ የዕውቀት፤ የፋይናንስና የአፈጻጸም አቅምን ማጎልበትን ያካትታል። የማዕከላዊ ጽሕፈት ቤትን ማጠናከር፤ የክልል ጽ/ቤቶችን መክፈትና በሰው ኃይልና በቁሳቁስ ማጠናከር፤ የአባላትን ቁጥር ማበራከትና ዕውቀታቸውንና ተሳትፎአቸውን በማጎልበት ለድርጅቱ አበይት ሥራዎች ማዘጋጀት ከአጣዳፊ ሥራዎቻችን ዋናዎቹ ናቸው።

አንድነት የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በሃገራችን ትርጉም ያለው ኢንዲሆን የበኩሉን ጥረት ያደርጋል። ምንም እንኳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምሥረታን፤ ፕሬስንና የሲቪል ማህበራትን የሚመለከቱ ሕጎች የመንቀሳቀሻ መድረኩን ክፉኛ የሚያጠብቡ ቢሆኑም በሕጋዊነት፤ በዕውቀት፤ በጥበብ፤ በቀና አመለካከት፤ በትዕሥትና በጠነከረ መንፈስ በመሥራት ታቅዶ የጠበበውን መድረክ እንዲሰፋና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን የማስፈን ተስፋ እየለመለመ እንዲመጣ ማድረግ ይቻላል ብሎ አንድነት በጽኑ ያምናል። መንግሥትም በእልክ መንፈስ ውስጥ በመግባት በአሳሪ ሕጎች የፖለቲካ መድረኩን ከማጥበብ ይልቅ በማስፋትና በማስተካከል የሃላፊነት ባህሪይን በሚያሳይ መልክ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ አንድነት ጥሪውን ያቀርባል።

በመጨረሻም አንድነት የመንግሥትም ሆኑ የግል መገናኛ ብዙሓን ራሱን የሚያይባቸው እውነተኛ መስተዋቶች እንዲሆኑና እነሱን በማየት ራሱን እያስተካከለና እያሻሻለ ለመሄዱ ምክንያቶች እንዲሆኑት ይፈልጋል። በርዕሰ አንቀጾቻችሁ፤ በዘገባዎቻችሁና በተለያዩ ዓምዶቻችሁ ከምትሰነዝሯቸው የሰሉ ሂሶችና ሃሳቦች ለመማር ዝግጁ መሆኑንና የሕዝቡን የመረጃ ፍላጎት ለማርካት በምታደርጉት ጥረት አንድነት ተባባሪያችሁና በሩም ለሁላችሁም ክፍት እንደሆነ ያረጋግጥላችኋል።

የሕዝብ መሠረት ያለው ሠላማዊ ትግል ያሸንፋል!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ፓርቲ

መሰከረም 15 ቀን 2001

አዲስ አበባ።