ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው

ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው

ከጎልጉል ድረገድ

religions ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።

ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።

የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡ Continue reading